• No results found

Amharic abstract

N/A
N/A
Protected

Academic year: 2022

Share "Amharic abstract"

Copied!
2
0
0

Loading.... (view fulltext now)

Full text

(1)

Amharic abstract

ፍሬ-ነገር (አጠቃሎ)

ይህ አንብሮ ከፍተኛ ትምህርት ተኰር የቋንቋ ፖሊሲ አንኳር ጥያቄዎችን በማሸጋገር በኩል ምክንያት የሆኑ ገዢ ዘይቤዎችን (ተረኰችን) ይመረምራል፡፡ ጥናቱ የተካሔደው በአገር አቀፍ ደረጃ ሪፖርቶችንና የመንግሥት ሰነዶችን፣ በተቋም ደረጃ ደግሞ በስዊድን ምሣሌ የዩንቨርስቲ የቋንቋ ፖሊሲን በመውሰድ ነው፡፡ የምርምር ጥያቄዎች በቋንቋ መርሆችና እውቀቶች ላይ ያተኩራሉ፡፡

ግኝቶቹ እንደሚያሳዩት የኢኮኖሚ/የገበያ፣ የአካታችነትና የስኬት ዘይቤዎች አንዱን ከሌላው መለየት በማይቻልበት ደረጃ ርስበርስ ተሸምነው ቋንቋዎች በምንና እንዴት እንደሚመዘኑ፣ ባለሙያዎችና ተማሪዎች እንደምንያሉ የቋንቋ እውቀቶች እንደሚፈልጉ መወሰን ችለዋል፡፡ ኢኮኒሚያዊ ምክንያትና የገበያ ዋጋ የቋንቋንምንነት በመተርጐምና በዚያውም የተሳትፎንና የብልጽግናን ደረጃ በማጽናት ጐልህ ሚና እየተጫወቱ መምጣታቸውን ግኝቶች ይጠቁማሉ፡፡

የቋንቋ መርሆች ተደርገው የተወሰዱት በዋናነት የስዊድንኛና እንግሊዝኛ ስዩማዊ (ማለትም እንደ አቻ ቋንቋዎች) ቋንቋዎች ናቸው፡፡ ስዊድንኛ በብሔራዊ ቋንቋነቱ በደኅንነትና በዲሞክራሲያዊ ምክንያቶች አስፈላጊ፤ የምሁራን የሳይንስ ቋንቋ ጠባቂዎችና የሳይንስ ትምህርት አስተናባሪዎች ቋንቋ ሆኑዋል፡፡ እንግሊዝኛ በዐለም ቋንቋነቱ ለሊበራል ምርምርና ለገበያ-መር ትምህርት አስፈላጊ ወይም የማይታለፍ ተብሏል፡፡ በሌላ በኩል ግኝቶቹ ለወንድማማችነትና ለዐለም-አቀፋዊ ኃላፊነት በሚሉ አመክንዮዎች ተመራጭ ሆኖ ይታይ ከነበረበት ከ1970ዎቹ ሽግግር ማድረጉንም ያመለክታሉ፡፡ እንደ ታዋቂና ተፈጥሯዊ የውጭ ቋንቋነቱ ለሙያ፣ ለሕገ-አልዮትና ለተሳትፎ ተገቢ ሆኖ ተወስዷል፡፡

ግኝቶች እንደሚያመለክቱት በ2000ዎቹ ከፍተኛ ትምህርት የእንግሊዝኛ-ስዊድንኛ ሁለት-ልሳንነት እንጂ ልሳነ-ብዝሃነት ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ አልነበረም፤ የኅዳጣን ወይም የመጤዎች ቋንቋዎችም እንዲሁ ከከፍተኛ ትምህርት ጋር በተያያዘ ቅቡልነት አልነበራቸውም፡፡ ለልሳነ-ብዙ ተማሪዎችና ምሁራን እምቅ የቋንቋ ተሰጥኦ እውቅና ከመስጠት ይልቅ እንደጉድለት የማየት እሳቤ በሰፊው አለ፡፡ የውጭ ተማሪዎችና ምሁራን በእንግሊዝኛና በእንግሊዝኛ ብቻ የተራቀቁ ሆነው ተወስደዋል፡፡ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች ለዩንቨርስቲዎች አስፈላጊሆነው ተስለዋል፡፡ የገበያ ዋጋና ኃይሎች በእነኝህ ተማሪዎች አማካኝነት ለተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ለዩንቨርስቲዎችም ስኬት እንዳመጡ ይታሰባል፡፡

በስዊድን ዩንቨርስቲዎች የቋንቋ ፖሊሲ የቋንቋ ታሳቢዎችና እውቀቶች የተካተቱበት አሰራር ከአገሪቱ ደረጃ ጋር የሚናበብ መሆኑን ግኝቶች ያስገነዝባሉ፡፡ የስዊድንኛና የእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የአቻነት መርህ ስዊድንኛን እንደዋነኛ ቋንቋ ወስዶ፣ እንግሊዝኛን የትምህርት ደረጃ ከፍ ባለ ቁጥር ወሳኝነቱ የሚጨምር አድርጐታል፡፡ ተማሪዎችና ባለሙያዎች እንደ ቋንቋ አስተማሪዎች ሁሉ የቋንቋ መሻሻል ያሳያሉ የሚል እሳቤ በሰፊው ይንጸባረቃል፡፡ የቋንቋ መርሁም በአመዛኙ ከዘወትር-ቋንቋ ንቅናቄ አንጻር የተቃኘ

(2)

ቢሆንም ቋንቋን ከሕዝቦች በመነጠል ተቀጥያ፣ መሳሪያ ወይም ቴክኒካዊ ያስመሰሉት የማፍረስና የመስራት ሒደቶችም የራሳቸውን ሚና ተጫውተዋል ማለት ይቻላል፡፡

በመጨረሻ የግኝቶቹ አንደምታዎች ከትምህርታዊ ስራዎች ጋርበ ማሰናሰል ተገልጸዋል፡፡

References

Related documents

U sing norms identified by Manners in his article "Normative Power Europe: A Contradietian in Terms?" (2002) as the tools when analysing CFSP-staternents both from

Influence of groove width on affinity for bone formation and stability of grooved oxidized screw-shaped titanium implants.. A biomechanical and histological study in

In Chapter 4, the numerical methods used in the thesis are presented: Newtons method, for solving the forward and adjoint problems; the conjugate gradient method (CGM) for finding

På små värmeföretag, med en panna på 10-20 MW och stödanläggningar, kan personalen be- stå av en värmechef, som även ansvarar för distributionen/försäljningen av värme och

Ett aktivt arbete för att se till att information inte skickas ut i stora massutskickade block utan istället via specifikt adresserade e-mail skulle underlätta situationen

Detta arbete fokuserade på dessa modifikationer skulle optimeras för just båten Albin 25 men som kan ses i Bilaga 1 finns många olika typer av lösningar med olika

For the Priced WDP model test results indicate that the higher the number of single instrument orders the greater the difficulty of the input is3. The interpretation of this effect

In this thesis, we undertook the problem of compressing trained deep learning models without causing any significant loss in performance measured using test set inference accuracy.